የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዳግም ሲጀምር አራት ጨዋታዎችን ቢቢሲ ስፖርት በነፃ እንዲያስተላልፍ ፈቃድ አገኘ። ቢቢሲ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች እንዲያስተላልፍ ፈቃድ ሲያገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሐሙስ እለት ይፋ እንደተደረገው ከሆነ ምንም እንኳ የመንግሥት ፈቃድ እየተጠበቀ ቢሆንም ጨዋታው ሰኔ 10 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል። " ይህ እድል ለቢቢሲና ለተመልካቾቹ ትልቅ እድልን ይፈጥራል"ያለችው የቢቢሲ ስፖርት ዳይሬክተር ባርባራ ስላተር ናት። የመጀመሪያው ጨዋታ በአስቶን ቪላ እና በሼፊልድ ዩናይትድ ፣ ማንቸስተር ሲቲ ከአርሴናል ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።