•  05/30/2020 02:06 PM

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 95 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ***************************** ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5034 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና አምስት (95) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ሻይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,063 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 71 ውንድ እና 24 ሰት ሲሆን የዕድሜ ክፈላቸው ከ 15 እስከ 80 ዓመት ውስ ጥ ይገኛል። በዜግነት ዘጠና አራት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እንደ የህንድ ዜጋ ይገኛል። 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሶስት (3) ሰዎች ከትግራይ ክልል አንድ (1) ሰው ከአፋር ክልል ፣ አምስት (5) ሰዎች ከአማራ ክልል፣ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሐረር ክልል፣ ሁለት (2) ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሶስት (3) ሰዎች ከሶማረ ክልል ናቸው። የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ • የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው 30 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው 4 •የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው 61 በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አንድ (11) ሰምች (ሁለት ከትግራይ ክልል እና ዘጠኝ ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገግ ሙ ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ስምንት (208) ነው

  •  05/30/2020 10:10 AM

#MoHEthiopia የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ከ03/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው። ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ ነው ተብሏል። አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ መስተዋሉ ተገልጿል ። በመሆኑም ወጥ በሆነ ጋይድ ላይንና ቼክሊስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል ይጎበኛሉ ድጋፍም ይደረግላቸዋል ተብሏል። ይህ ድጋፋዊ ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን ይኖርበታል ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ - #ENA

  •  05/30/2020 10:08 AM

በጣልያን በአንድ ቀን 8,014 ሰዎች አገገሙ! በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8,014 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ማገገማቸው ሪፖርት ተደርጓል። (ይህ ቁጥር እስካሁን ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው) በሌላ መረጃ የሟቾች ቁጥር ትላንት ከተመዘገበው ጨምሯል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ369 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። በተጨማሪ 1,444 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ጣልያን ለወራት ተጥሎ የነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ እየላላ በመሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ወደ እንቅስቃሴ እየተመለሱ ይገኛሉ።

  •  05/30/2020 10:06 AM

#COVIDO_ORGANICS ምንም እንኳን የዓለም ጤና ድርጅት ሰዎች ለኮቪድ-19 ህክምና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ ባህላዊ መድሃኒቶችን እንዳይጠቀሙ ቢያስጠነቅቅም የማዳጋስካርን መድሃኒት ፈላጊ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው። ደቡብ ሱዳን በማዳጋስካር ፕሬዘዳንት አንድሪ ራጆሊና የተዋወቀውን የኮሮና ቫይረስ ባህላዊ መድሃኒትን ወደ ሀገሯ ለማስገባት ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል። በሌላ በኩል ማዳጋስካር ከሳምንታት በፊት አገኘሁት ብላ ባሳወቀችው የኮቪድ-19 መድሃኒት ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ንግግር መጀመሩም ተሰምቷል።

  •  05/30/2020 10:03 AM

ስፔን ? በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር አሳይቷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት 244 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር 25,857 ደርሷል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 3,121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 253,652 ከፍ ብሏል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ነገ እንዲህ ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይገመት ፤ የስርጭትና የመስፋፋት ፍጥነቱ እጅግ አደገኛ ነውና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!

  •  05/30/2020 10:00 AM

-ሬድቡል ሳልዝበርግ የኦስትሪያ ዋንጫን በባዶ ስታዲየም አነሳ! -ሊቨርፑል ከ30 አመት በኋላ የፕርሜር ሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ በዝግ ስታዲየም ሊያነሳ ነው?

  •  05/29/2020 05:08 PM

#MutahiKagwe በኬንያ በአንድ ቀን 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ! በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት አርባ ሰባት (47) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 581 ደርሷል። በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 8 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 190 ደርሷል። እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 26 ደርሷል።

  •  05/29/2020 04:57 PM

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት (137) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት (968) ደርሷል፡፡

I BUILT MY SITE FOR FREE USING