ዲያጎ ሲሞኔ ካለ ቶማስ ፓርቴይ የአትሌቲኮ ማድሪድን አማካይ ክፍል ለማዋቀር ከወዲሁ እየተሰናዳ ነው። ለናፖሊው ብራዚላዊ አማካይ አለን ዝውውር ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ለሙንዶ ዲፖርቲቮው ማውሮ አራምባሪንም ለማስፈረም በመንቀሳቀስ ወደ አርሰናል ይዛወራል ተብሎ ለሚጠበቀው ጋናዊ አማካይ ምትክ በማድረግ ሊያስፈርማቸው አስቧል።