•  05/30/2020 10:10 AM

#MoHEthiopia የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ከ03/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው። ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ ነው ተብሏል። አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ መስተዋሉ ተገልጿል ። በመሆኑም ወጥ በሆነ ጋይድ ላይንና ቼክሊስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል ይጎበኛሉ ድጋፍም ይደረግላቸዋል ተብሏል። ይህ ድጋፋዊ ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን ይኖርበታል ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ - #ENA

  •  05/30/2020 10:03 AM

ስፔን ? በስፔን የሟቾች ቁጥር መጨመር አሳይቷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት 244 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር 25,857 ደርሷል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 3,121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 253,652 ከፍ ብሏል። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ነገ እንዲህ ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይገመት ፤ የስርጭትና የመስፋፋት ፍጥነቱ እጅግ አደገኛ ነውና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ!

  •  05/30/2020 10:00 AM

-ሬድቡል ሳልዝበርግ የኦስትሪያ ዋንጫን በባዶ ስታዲየም አነሳ! -ሊቨርፑል ከ30 አመት በኋላ የፕርሜር ሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ በዝግ ስታዲየም ሊያነሳ ነው?

I BUILT MY SITE FOR FREE USING