•  05/30/2020 02:06 PM

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 95 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ***************************** ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5034 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና አምስት (95) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ሻይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,063 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 71 ውንድ እና 24 ሰት ሲሆን የዕድሜ ክፈላቸው ከ 15 እስከ 80 ዓመት ውስ ጥ ይገኛል። በዜግነት ዘጠና አራት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እንደ የህንድ ዜጋ ይገኛል። 56 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሶስት (3) ሰዎች ከትግራይ ክልል አንድ (1) ሰው ከአፋር ክልል ፣ አምስት (5) ሰዎች ከአማራ ክልል፣ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሐረር ክልል፣ ሁለት (2) ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሶስት (3) ሰዎች ከሶማረ ክልል ናቸው። የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ • የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው 30 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው 4 •የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው 61 በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አንድ (11) ሰምች (ሁለት ከትግራይ ክልል እና ዘጠኝ ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገግ ሙ ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ስምንት (208) ነው

  •  05/30/2020 10:10 AM

#MoHEthiopia የጤና ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች ከ03/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ ድጋፋዊ ክትትልና ጉብኝት ሊያደርግ ነው። ድጋፋዊ ክትትሉ በዋናነት የሚደረገው ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ውጭ ባሉ መደበኛ ስራዎች ላይ ነው ተብሏል። አሁን ባለው ሁኔታ ከሆስፒታል እስከ ጤና ኬላዎች በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት በመደበኛ የሕክምና ስራዎች ላይ ከፍተኛ መቀዛቀዝ መስተዋሉ ተገልጿል ። በመሆኑም ወጥ በሆነ ጋይድ ላይንና ቼክሊስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ጤና ተቋማት አሰራር በምን ሁኔታ ላይ እንደሆኑና የቢሮ አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስል ይጎበኛሉ ድጋፍም ይደረግላቸዋል ተብሏል። ይህ ድጋፋዊ ጉብኝት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የመደበኛ ሕክምና አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ከተቻለም ከዚያም ለማሻሻልል መከናወን ይኖርበታል ብለዋል ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ - #ENA

  •  05/29/2020 04:57 PM

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት (137) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት (968) ደርሷል፡፡

I BUILT MY SITE FOR FREE USING